Wednesday, April 30, 2014

ዱላ፣ጥይት፣ግድያ፣እስራትና ወዘተ መልስም ጥያቄም አይሆንም! ከአፄ ምኒሊክ ዘመነ መንግሥት አንስተዉ እስከ ዛሬ ድረስ ከባዕዳዉያን ጋር የተሰለፍት የኦሮሞ ተወለጆች ለምንድነዉ ተማኝ የፈረስ ጋሪ የሚሆኑት?


    
እዉነት እዉነት እላችኋለሁ ይላል ኢየሱስ ክርስቶስ ሲናግር፤ወንጌል መስበኬ አይደለም፣የኢየሱስ ክርስቶስ የቃላት አጠቃቀም ተመችቶኝ ነዉ እንጂ፡፡ ስለ አዲስ አበባና ስለ አዲስ አበባ ልዩ ዞን ዙሪያ ያለኝን ሀሳብ መግለጽ ፈልጌ ነዉ፡፡ ወደ ሙሉ ዝርዝር ሳልገባ በፍት፣ እኔ የቁቤ ተማሪ ነኝ፣ የቆሎ ተማሪ እንደሚባለባዉ ሁሉ፡፡አማርኛ ሁለተኛ ቋንቋዬ ነዉ፤ነገር ግን የሳልስን፣የሳድስን፣ የቃለት አጠቃቀምንና ወዘተ ግድፈቶችን ካሳየሁኝ ይቅረታ እንድደረገልኝ ከአሁኑ አሳስባለሁኝ፡፡ ይህን ሲል ግን ሀሳቤን በአማርኛ መግለጽ አልችልም ማለቴ አይደላም፡፡ዘጠና ዘጠኝ ፐርሰንት ሙሉ በሙሉ ንብረቴን የሆነዉን ቋንቋዬን ሳጥን ዉስጥ አስቀምጬ፣ ዘጠና ፐርሰንትን ባተረፍኩት በትርፍ ቋንቋዬን ሀሳቤን መገለጽ እችልዋለሁ ማለቴ ነዉ፡፡

በአፄ ምንልክ የሚመራ ነፍጠኞች ወደ ሸገር(አዲስ አበባ፣ፍንፊኔ) ሲመጡ፣ ሸገር ምን፣የማን፣ዬት እንደነበረች ማንበብና መጻፍ የምንችል፣ እንደሁም ታርክን ከሚያዉቁት አባቶቻችን የሰማነዉ ማወቅ እንችላለን፡፡ አፄ ምንሊክ ማንናቸዉ? እንዴትስ ወደ አዲስ አበባ መጡ?  በምን በሽታ ሞቱ? እንድሁም በአፄ ምኒሊክና በሆራ ፍነፍኔ (በፍነፍኔ ዉልዉሃ) ጋር ያላቸዉ ግንኙነት ምንድ ነዉ?  ለምን  የፍነፍኔ ዉልዉሃን አማራጫቻዉን አደረጉ? ምኒልክ ወደ አዲስ አበባ ሳይመጣ በፊት አዲስ አበባ ምን ትባል ነበር?  አዲስ አበባ እንዴት አዲስ አበባ ተባለችና ወዘተ  የሚባሉት ጥያቄዎችን  ለታርክ ተመርማርዎቸች እተዋለሁኝ፡፡ ጉሌለ ማለት ምን ማለት ነዉ? የካ ማለት ምን ማለት ነዉ? ላፍቶ ማለት ምን ማለት ነዉ? ቀበና ማለት ምን ማለት ነዉ? ባካኒሳ ማለትስ ምን ማለት ነዉ? ቦሌ ማለት ምን ማለት ነዉ? እዉነት እዉነት እላችኋለሁኝ፣ መጽሐፍ ቅዱስ  እንዳለሁ እየሱስ ክርስቶስ ለሰዎች ሓጥአት ሲባል ያለምንም እንከን የተሰቀለ ጌታ ነዉ፡፡ በኔ ሀሳብ መሰረት የኦሮሞ ህዝብ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰዎች ሓጥዓት ሲል እንደ ሞተ ሁሉ፣ለነፍጠኞች ሲል ሞቷል፡፡

የኦሮሞ ሕዝብ እንዴት ለነፍጠኞች ሞቴ ለምለዉ ጥያቄ፡ አንደኛ፣ ምኒልክ የኦሮሞን ህዝብ ያስገዛዉ ለብቻቸዉ አልሰበረም፣በመጽሓፍ ቅዱስ አገላለፅ ያሁዳ በተበሉት ሻጭዮች ራስ ጎበና ዳጪን ተጠቅሞ ነዉ የኦሮሞ ሕዝብን ያስገበሩት፡፡ ማስገበር ብቻ ሳይሆን የኦሮሞን ሕዝብ በግማሽ ቁጥር ጨፍጭፏል፤ እንዱሁም ሌሎች ጭቁን ብሔሮች ተጨፍጭፏል፡፡ ዓጼ ምኒልክ ኦሮሞን  ሲጨፈጭፍ የብሔር ሻጮች የሆኑት እንደነ ራስ ጎበና ዳጪን ተጠቅሞ ነዉ የኦሮሞ ሕዝብን የሰበሩት፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ለምንድነዉ ተማኝ የፈረስ ጋሪ የሚሆነዉ? ራስ ጎበና ዳጪ ታዋቂ ተዋጊና የአባ ገዳ ልጂ እንደ ነበረ ታርክ ያወገናል፡፡ ነግር ግን ራስ ጎበና ዳጪ ከምኒሊክ ጋር ተመሳጥሮ ለኦሮሞ ህዝብ ጀርባዉን ሰጥተዉ ለምኒልክ ተማኝ ተዋጊ ሆነዉ ሸዋ (ቱለማን)፣ አርሲን፣ እቱ አፈረን ቃሎ (ሀረጌን)፣ ባሌን፣ ጉጂን፣ቦለናን፣ ወለይታን፣ጋሞ ጎፋን፣ከፈን፣ ደቡቦችና ወዘተን  ሰብረዉ ከምኒልክ ግዛት ሥር ያስገባዉ ታዋቂዉ የኦሮሞ  የፈረስ ተዋጊዉ ራስ ጎበና ዳጪ እንደነበሩ ከታርክ ማህደር ማወቅ ችለናል፡፡ ታዋቂዉ የፈረስ ተዋጊዉ ራስ ጎበና ዳጪ ይህንን ዉለታ ሁሉ ሲዉል ከምኒሊክ ምንስ ሽልማት ተሰጣአዉ? ራስ ጎበና ዳጪ እነዴት ሞቱ? አጼ ምኒሊክ ለምንስ ራስ ጎበና ዳጪ እስክሞት ድረስ  የንጉሰ ነግስታት ዘዉድ አልደፉም ነበረ? ራስ ጎበና ከሞተ በኋለ አጼ ምኒሊክ ለምንስ የንጉሰ ነግስታት ንጉስ ሆነዉ ዘዉድ የደፉት? እኔ ጋዜጠኛዉ  ይሄንን ጥያቄ በሙሉ ለታርክ ተመርማርዎች ትቸዋለሁኝ፤ታርክ ታርክ ነዉና፡፡

አጼ ምኒሊክ የአዉሮፓዉያን የጦር መሳሪያ ተጠቅሞ የዉሸት ቃል ኪዳን ዉል ከፈረስ ተዋጎቹ ጋር  ተዋዉለዉ   ከሰሜን ሸዋ ወደ ደቡብ ኢትዮያና ወደ ሌሎቹ የኢትዮያ ክፍሎች ግዛታቸዉን ማስፋፋቱ ይታዎሳል፡፡ ይህ በእንድ እንዳለ፣ አጼዎቹ ሴት ልጆቻቸዉን  ለፈሩት ሰዉ እየዳሩ እንደ ብር ለግዛታቸዉ ሲሉ እንደ እቃ በስልጣን ሲለዉጡ ተስተዋዉለዋል፡፡  በሌላ በኩል ደግሞ አጼ ምኒሊክ ለአዉሮፓዉያንና ለአሜርካዉያን የኢትዮፕያን ልጆች ለባሪያ ንግድ እየሸጡ በለወጡት በጦር መሳሪያ ኦሮሞዎችን፣ ደቡቦችን፣አፋሮችን፣ሱማሌዎችንና ወዘጸ በጦር መሳሪያ ለዉጣቿል፣ እንዲሁም ባገኘዉ በጦር መሳሪያ ደግም ኦሮሞዎችን፣ ደቡቦችን፣አፋሮችን፣ሱማሌዎችንና ወዘተ ጨፍጭፈዉበታል፡፡ በምስራቅና በደቡብ ኢትዮያ አርሲ (አኖሌ) ፣አፈርን ቃሎ(ሀርረጌ ጨለንቆ አከባብ)፤ባሌ፣ ጉጂ፣ቦረና፣ ወለይታና ወዘተ ከፍጠኞቹ ጋር ተጋፍጠዉ እጃቸዉን፣ ጡታቸዉን፣ ብልታቸዉንና ወዘተ ሲቆረጡ፣ምዕራብ ኦሮሚያ ላይ እነ አባ ጂፋር ለምኒሊክ እጃቸዉን መስጠታቸዉ ለኦሮሚያ ዉድቀት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ተጫዉተዋል፡፡ ይሄንን የመሰሌ የታረክ ግድፈቶችን የማያዉቁ አንዳንድ  የኢትዮጵያ አዝማረዎች  አጼ ምኒሊክ ኢትዮያን አንድ ለማድረግ ያደለጉት ጦርነት ቅዱስ ጦርነት ነዉ  እያሉ ይገኛሉ፡፡  
        
ከአፄ  ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ወደ አፄ ሐይለሥለሤ  ዘመነ መንግስት ሲንመጣ፣ ጀኔራል ታደሴ ብሩ በአፄ ሐይለሥለሤ ላይ የተቃጣዉን  መፈንቅለ መንግስት ካከሸፈ በኋላ ምን አይነት ሽልማት  ከአፄ ሐይለሥለሤ  መንግሥት አገኘ? ጣልያን ኢትዮያን ሲትወሪ አፄ ሐይለሥለሤ ወደ እንግሊዝ ሲሸሹ ከጣልያኖች ጋር የተጋፈጡት ማንናቸዉ? እነ አገሪ ቱሉ፤ እነ አብዲሳ አጋ፤እነ ባልቻ አባ ነፍሶ፣ ወዘተ ማን ናቸዉ? ከነፍጠኞች ጋር የተሰለፉ አሮሞች የዉሃ ሽታ ሆነዉ ለምን ቀሩ? አመጣጣቸዉ ከገዳ ሥርዓት ስለ ሆነ አይፈረድባቸዉም፡፡ የገዳ ሥርዓት ድሞኪራሳዊነት፡ እኩልነትና ታማኝነት ስለሚታይበት ዘመኑ ያልደረሰበት ከነፍጠኞቹ ርቀዉ ታማኝ ሆነዉ ተገኙ እንጂ ቃልኪዳናቸዉም ባይጠበቅላቸዉም የተሸወዱ አይመስለኝም፡፡ ሆነዉም ግን ከባዳዉያን ጋር መሰለፍ፣ የአሮምኛ ተረት እንድምለዉ “namni diinaaf gubate daaraa hin qabu” ትርጉሙም ለጠላት የተቃጠለ ሰዉ አመድ የለዉም ማለት  ነዉ፡፡ በተመሳሳይ፣ከአጼ ምኒሊክ ዘመነ መንግሥት እስከ አጼ ሓይለሥላሤ ዘመነ መንግሥት ድረስ ከነፍጠኞች  ጋር የተሰለፉት አሮሞች ያገኙት ምስጋናና ማዕረግ ብኖር መርዝ መጠጣት፣መገደል፣መሰቀል፣ ተራ የሆነ ስልጣን ማግኘትና፣ወዘተ ነዉ፡፡

የደርግ መንገስትም ደግሞ ቀንደኛ የሶሻልዝም አራማጅና ባንድ ኢትዮጵያ ሥም የሚነግድ፣ ጨካኝ ገዳይ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ሆኖም ግን በደን ተከላና የቀበሌ ቤቶችን ሰረተዉ ለደሃዎች ለማከፋፍል ከዛሬዉ የመንግሥት ኮንዶሚዬም በለይ ተወዳጅነት አፍርተዋል፡፡ የዛሬዉ የመንግሥት ካደሬዎቹ ግን በደርግ መንግሥት የተሰጣቸዉ የቀበሌ ቤቶችን  በእንቨስትመንት ሥም ከደሃዉ ሕብረተሰብ  እየቀሙ ሲቸበእቡና ለራሳቸዉ ሲኖሩበት ደሃዉ ሕብረተሰብ መጠልያና መቅመሻ አጥተዋል፡፡

ኦሮሚያ ዉስጥ ከተሞች በነፍጠኞች ሲቆረቆሩ የኦሮሞ ሕዝብ ላለፉት ለመቶ ዓመታት ከቄኤዉ፣ከቤት ንብረቱ ሲፈናቀል ቆይቷል፡፡ በኦሮሚያ ዉስጥ ከተሞችን የቆረቆረዉ ነፍጠኞች ነዉ እንጂ የኦሮሞ ሕዝብ አይደለም፡፡ ዛሬም ብሆን የኦሮሞ ሕዝብ በኦሮሜያ ዉስጥ ከሚገኙት ከተሞች እያገኘ ያለዉ ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ ይበልጣ፡፡ ሲጀመር ራሱ ኦሮሞን ልጎዱበት ነዉ እንጂ ልጠቅሙበት አይደለም ከተሞችን በኦሮሚያ ዉስጥ የቆሮቆሩት፡፡ በኦሮሚያና በሌሎች ክልሎች ዉስጥ የሚገኙት ከተሞች አመሠራረታቸዉ ለነፍጠኞች ሠራዊቶች ሲባል  ከአዉሮፓ  ባገኙት ነፍጥ (በዘመናዊ የጦር መሣሪያ) የአከባብን ሁኔታ ከቁጥጥራቸዉ ስር  አስገብተዉ  ከሠፈሩበት በኋላ ነገሩ ከተመ ወይም ከተማ አሉት፡፡ እነርሱ ሲሰፍሩበት ጊዜ ያ ቦታ የማን ነበር? እነማን ከዛ ተፈናቀሉ? እንዴት ተፈናቀሉ? ካሣ ተከፈላቸዉ ወይስ ሙት ተከፈለቸዉን? ወዘተ ለታሪክ ተመራማሪዎችና ዓዋቂዎች ልተዉና ወደ ዋና ቁምነገረ ልመለፍ፡፡ የአዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ዞን ጉዳይ በወሬ ደረጃም ሲንሰማ ቆይተናል፡፡ የአዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ዞን ጉዳይ በአባ ዱላ ዘመነ መንግሥት ጊዜ አድስ አበባ ወደ ጎን እየሰፈች  የኦሮሞ አርሶ አደሮችን ከመሬት፣ከቤት ንብረቱ፣ከቋንቋዉ፣ከማንነቱና ወዘተ እንዳታፈናቀላቸዉ ትኩረት ተሰጥቶበት በኦሮሚያ ሥር አንዲትተዳደር ተገረጎ ነበረ፡፡

ያሁሉ ቀረና፣ አሁን ግን በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉት ከተሞችን ከአዲስ አበባ ጋር በልማት እናስተሳስራለን እያሉ ብቅ ማለት ጀመሩ፡፡አንድ የኦሮሚኛ ተረት እንደሚለዉ  leenci rafe waan du’e fakkaata  ትርጉምም የተኛ አንበሳ የሞቴ ይመስላል እንደሚባለዉ ሁሉ፣የኦሮሞ ገበሬዎች ከቄኤያቸዉ፣ከቤት ንብረታቸዉ፣ ወዘተ ሲፈናቀሉ በኦሮሞች ዉስጥ ያለዉ ወኔና ልብ የማይቆጣ መስሎአቸዉ  የመንግሥት ካድሬዎች፣  ወደዳችሁም ጠላችሁም የአዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ዞን ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ስር ወጥተዉ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ስር መግባት አለበት አሉ፡፡ ይህች ለአዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ዞን ለምን አለቀሱላት?  እዉነትም ለልማት ነዉ? በኦሮሚያ ሥር መልማት አትችልም? አንድ የመንግስት ካድሬ ከአዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ዞን ብዙ መሬቶችን አልወሰደም? እነዚህ ካድሬዎች  ለአዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ዞን እድገት  ነዉ ወይስ ለጥቅማቸዉ ስሉ ነዉ የወተወቱት?  ኦሮሞች አዲስ አበባ ከተቆረቆች ወዲህ ምን አተረፉ? ከአዲስ አበባ አከባቢ ከተለያየ ፋብርካ የሚወጣ መርዛማ ኬሚከሎች  ወደ ወንዞቹ ገብተዉ ሲበክል፣ የሰዉንና የእንስሳትን ነፍስ ሲያጠፋ፤በእንቨስትመንት ስም የኦሮሞ ገበሬዎች ከመሮታቸዉ ተፈናቅለዉ ተመልሰዉ ለባለሀብቶቹ በመሬታቸዉ ላይ እንደ ባሪያ እንደገና ጉልበታቸዉ ሲበዘበዝ፤የኦሮሚኛ ቋንቋ፣ባህል፣እሴትና ወዘተ ሲበዘበዝ፤በኢፈዲረ ሕገመንግስት ዓንቀጽ 49/5 ላይ የኦሮሞ ሕዝብ ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ማግኘት አለበት የሚለዉ ወደ ተቃራኒ ሲለወጥ፤ በአባ ዱላ ጊዜ በአዲስ አበባ ዉስጥ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በኦሮምኛ የሚያስተምሩ ት/ቤቶች ለመክፈት መሬት ተዘጋጅተዉ አጥር ታጥሮበት የነበረ ከአባ ዱላ ጋር መጥፈቱንና ወዘተ፣ እዉነት እዉነት እላችኋለሁ ይህ ሁሉ ሕዝብን አቃጥቷል፡፡

ከሰማንያ በላይ ብሔርና ብሔረሰቦች በሚኖሩባት ሀገር ዉስጥ ለአንድ ብሔር ብቻ የወገነ መንግስት፣የኢትዮጵያ ብሔርና ብሔረሰቦችን ለምን እየጋበዜ ይሁን? አንዱ ከሌላ  ቦታ መጥተዉ በገዛ መሬታችን  ላይ ቱጃር ሲሆን፣ እኛ ደግሞ በተቃራን ቁልቁል ስንሄድ፣ የመንግሥት ከፈተኛ ካድሬዎች በተለይ የትግይ ተወላጆች የፖለትካ ኢኮኖሚን ተጠቅሞ ቁልፍ ሥልጣን ሲይዙ፣ቁልፍ ቦታ ሲይዙ፤የአገሪቱን  ንብረት ከቁጥጥራቸዉ ስር ሲያስገቡ፣የኬላ ጠባቂዎችና ታማኞች የትግራይ ተወላጆች ብቻ ሲሆኑ፣ በአገር መከላኪያ ሥም የትግራይ ተወላጆች ተሰባስበዉ ልዩ ጥቅም ሲያገኙ፣ ሌሎች ብሄርሮች በተለይ ሲጨቆኑ የነበሩ በኢኮሚ ጠነ መመታታቸዉ፣ የትግራይ ካምፓኒዎች ኢትዮጵያ በሙሉ ያላት ሀብት በለይ መሰብሰባቸዉን፣በጉጂ ዞን  በዓመት 4.1 ቶን ወርቅ የሚመረትበት ለጋ ደንብን ለሼክ መሀመድ ሁሴን አሊ አልሙድ የተሸጠዉ የወርቅ ማዕድን በስተጀርባ የትግራይ ተወላጆች ከፍተኛ ስልጣናት መኖራቸዉን፣ የከተማ መሬት አሰጣጥ ለተወሰነ ዓመታት ካቆሙ በኋላ በሊዚና በጨረታ እንድሰጥ ያመቻቹት ብር ያላቸዉና መግዛትም ሆነ መጫረት የሚችሉት እርነሱ ብቻ ስለ ሆኑ፣ በልማት ስም ለበአዲስ አበባ ዙሪያ ልዪ ዞን ተቆርቋሪዎች ሆነዉ ብቅ ማለታቸዉ ያልጠበቁት ተቃዉሞ ከኦሮሞ ተወላጆች ገጠማቸዉ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሄንኑን የተቃወሙ የኦሮሞ ተወላጆች የኦ.ሕ.ደ.ድ.  አባልም  ብሆኑም ከዛቻና ከእስር አላመለጡም፡፡ ፍለፊት አወጥተዉ የተናገሩትና የታሠሩት የመንግሥት ካድሬዎች ጥቂት ብሆኑም፣የኦሮሞ ተወላጆች የሆኑት የመንግሥት ሠራተኞች ዘጠና ስምንት ፐርሰንት የሚሆኑ አንጀታቸዉ አርሯል፡፡ ቀስ በቀስ ከመንግሥት መስሪያ ቤቶች የተጀመረ ተቃዉሞ ወደ የተለያየ ዩኒቨርሲቲዎች፣   ኮሌጆች፣ት/ቤቶች፣ከተሞችና ወዘተ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡በአሁኑ ጊዜ የተማሪዎችና የሕዝብ ተቃዉሞ ተስፋፍተዉ እየተከሄደበት ያለዉ ቦታ ጂማ  ዩኒቨርሲቲና ጂማ ከተማ፣ ሐሮማያ  ዩኒቨርሲቲና ሀረር አከባብ፣ ወለጋ ዩኒቨርሲቲና ናቃምቴ ከተማ ከነሁለተኛ ደረጃና መስተንግዶ ት/ቤቶች ጭምር፣ ምዕራብ ወለጋ ደንብ ዶሎ ከተማ፣ መቱ ዩኒቨርሲቲና መቱ ከተማ፣ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲና  በምዕራብ ጉጂ ቡሌ ሆራ ከተማ፣አዳማ ዩኒቨርሲቲና አደማ ከተማ፣ድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲና ድሬ ዳዋ ከተማ፣ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲና ወዘተ ይገኙበታል፡፡

በጣም የምገርም ነገር፣የዩኒቨርሲቲ  ተማሪዎች ዲሞኪራሳዊ በሆነና በሰለም መንገድ ጥያቄያቸዉን ሲያቀርቡ ያገኙት ምልስ ዱላ፣ድብደባ፣ጥይት፣ እስራትና ሞትን ነዉ፡፡ በዲሞኪራሲ ጥላ ሥር የሚነግድ  የኢትዮጵያ መንግስት አምባገነናዊ ሥራ የት እንደሚያደርሰዉ በቅርቡ የሚናይ ይሆናል፡፡ ያምሆነ ይህ፣ዱላ፣ጥይት፣ግድያ፣እስራትና ወዘተ መልስም፣ጥያቄም አይሆንም! በተለይ በአምቦ ከተማ ዉስጥ በዛሬዉ እለት (04/30/2014) ከአምባ ገነን መንግሥት ወታደሮች በተከፈተዉ ተኩስ ቁጥር ስፍር የሌለቸ ተማረዎችና  የአምቦ ከተማ ነዋረዎች እየተገደሉና መሆናቸዉንና የሟቾቹን ሬሳም ማንሳት አንዳልተቻለ     https://www.spreaker.com/user/ragabaa/breaking-news-live-reportinf-from-ambo?error=access_denied&error_code=200&error_description=Permissions+error&error_reason=user_denied#_=   በተባለዉ ኦንለይን ሬዲዮ መረጋገጥ ተችሏል፡፡ ይህ ኦንለይን ሬዲዮ በቀጥታ ስርጭት ከአምቦ ከተማ እንዳስተላለፈዉ  ከሆነ ከኦሮሞ ተወለጆች ፖሊሶች ትጥቅ ተፈትተዉ ማንነታቸዉ የማይታወቁ ወታደሮች የጅምላ ጨፍጨፋን እያከሄዱ መሆናቸዉንና የተኩስ ድምጽም በጆሮዬ ሰምቻለሁኝ፡፡ ከአፄ ምንልክ ዘመነ መንግሥት አንስተዉ እስከ ዛሬ ድረስ  ከባዕዳዉያን ጋር የተሰለፍት የኦሮሞ
ተወለጆች  ለምንድነዉ ተማኝ የፈረስ ጋሪ የሚሆኑት? በጠራራዉ ጸሓይ የኦሮሞ ሕዝብ ስጨፈጨፍ ኦ.ሕ.ደ.ድ. ዬታለ
?  ከኦሮሞ ተወለጆች ፖሊሶች ትጥቅ የፈታባቸዉ ለምንድ ነዉ? ከባዳዉያን ጋር የተሰለፈ ኦሮሞ መጨረሸዉ ለምንድነዉ የማያብረዉ?  የኦሮሞ ሕዝብ መች ነዉ ሻጪዎችና ያሁዳዎችን ከራሱ ዉስጥ አዉጥተዉ የሚያባርረዉ?

በተመሳሳይም፣ በአምቦ አከባብ ብቻም ሳይሆን  በምዕራብ ጉጂ በቡሌ ሆራ  ዩኒቨርሲቲና ከተማ፣ በድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣በባሌ መዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ፣ በወለጋ ዩኒቨርሲቲና ነቀምት ከተማ፣ተማሪዎችና ነዋሪዎች  ተጎርተዉ በየአከባቢዉ የሚገኙት ሆስፕታሎች መጨናነቃቸዉን ተሰምቷል፡፡ አሁንም ደግሜ እዉነት እዉነት እላችኋለሁ ዱላ፣ጥይት፣ግድያ፣እስራትና ወዘተ መልስም፣ጥያቄም አይሆንም!

ከዳንኤል ገ/መድህን አሬሪ፡፡                

0 Comments:

Post a Comment

Subscribe to Post Comments [Atom]

<< Home