Tuesday, May 6, 2014

የኦሮሞ ሕዝብ ፀረ-ልማት አይደለም፤እንዶሁም የኢትዮጵያ የልማት አባት ነዉ እንጂ፡፡

እንደሚታወቀዉ ከአጼ ምኒሊክ በብፊት የዛረዉቱ ኢትዮጵያ የዛሬ ቅርጽ አልነበራትም፡፡ በኦሮሚያም ሆነ  በሌሎች ክልሎች ዉስጥ የሚገኙት ከተሞች አመሠራረታቸዉ ለነፍጠኞች ሠራዊቶች ሲባል  ከአዉሮፓ  ባገኙት ነፍጥ (በዘመናዊ የጦር መሣሪያ) የአከባብን ሁኔታ ከቁጥጥራቸዉ ስር  አስገብተዉ  ከሠፈሩበት በኋላ ነገሩ ከተመ ወይም ከተማ አሉት፡፡አጼ ምኒሊክ ለአዉሮፓዉያንና ለአሜርካዉያን የኢትዮፕያን ልጆች ለባሪያ ንግድ በመሸጥ በለወጡት በጦር መሳሪያ ኦሮሞዎችን፣ ደቡቦችን፣አፋሮችን፣ሱማሌዎችንና ወዘተ በጦር መሳሪያ እየለወጡ፣ እንዲሁም ባገኙ በጦር መሳሪያ፣ የተለያዩ  የበፊቱ የኢትዮጵያን ግዛቶች እንደ ኦሮሞ፣አፋር፣ከፋ፣ዎላይታ፣ወዘተን በመስበር ዛሬይቱ ኢትዮጵያን ፈጠሩት፡፡  
  
አጼ ምኒሊክ የዛሬይቱ ኢትዮጵያን ሲፈጥሩ የአዉሮፓዉያን የጦር መሳሪያ በመጠቅም የዉሸት ቃል ኪዳን ዉልም  ከሌሎች እንደነ ጎበና ዳጪ  ጋር  ተዋዉለዉ   ከሰሜን ሸዋ ወደ ደቡብ ኢትዮያና ወደ ሌሎቹ የኢትዮያ ክፍሎች ግዛታቸዉን ማስፋፋቱ ይታዎሳል፡፡ ይህ በእንድ እንዳለ፣ አጼዎቹ ሴት ልጆቻቸዉን  ለፈሩት ሰዉ እየዳሩ ለግዛታቸዉ ሲሉ እንደ እቃ በስልጣን ሲለዉጡ ተስተዋዉለዋል፡፡  በሌላ በኩል ደግሞ አጼ ምኒሊክ ለአዉሮፓዉያንና ለአሜርካዉያን የኢትዮፕያን ልጆች ለባሪያ ንግድ እየሸጡ በለወጡት በጦር መሳሪያ ኦሮሞዎችን፣ ደቡቦችን፣አፋሮችን፣ሱማሌዎችንና ወዘተን ጨፍጭፈዉበታል፡፡ በሰሜን በኩል በትግራይና በወሎ አከባብ ብዙዎቹ በነፍጠኞች ተጨፍጭፏል፡፡በምስራቅና በደቡብ ኢትዮያ አርሲ (አኖሌ) ፣አፈርን ቃሎ(ሀርረጌ ጨለንቆ አከባብ)፤ባሌ፣ ጉጂ፣ቦረና፣ ወለይታና ወዘተ ከፍጠኞቹ ጋር ተጋፍጠዉ እጃቸዉን፣ ጡታቸዉንና ብልታቸዉን  ሲቆረጡ፣ምዕራብ ኦሮሚያ ላይ እነ አባ ጂፋር ለምኒሊክ እጃቸዉን መስጠታቸዉ ምኒሊክ   ሀይል እንድጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ተጫዉተዋል፡፡
 
የነፍጠኞች ወታደሮች የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦችን ለማስገበር ሲሉ ወደ ተለያዬ የኢትዮጵያ ክፍሌ አገሮች ዉስጥ ሲሰራጩ፣ የወታደሮች ካምፕ ይመሰርቱ ነበረ፡፡ ነፍጠኞቹ ግዛታቸዉን ሲያከትሙ ነዉ ከተማን የመሰረቱት፡፡ በኦሮሚም ሆነ በሎሎች ክልሎች ዉስጥ ከተማ ሲከተም በሃይል፣ በግዳጅ፣ በግድያ፣በቅሚያና በወዘተ ነዉ ከተማ የተከተመ፡፡ ነፍጠኞቹ ወደ ተለያዬ የኢትዮጵያ ክፍሌ አገሮች ዉስጥ ሲሰራጩ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑና የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይም የነበሩ፤በፊዉዳሊዚም ጊዜም ገበሬ ከሚያርሰዉ ምርት 1/3 ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሚሰጥ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ አማርኛ ቋንቋ በብዛት በኢትዮጵያ ከተሞች ዉስጥ ለሚነገርበት ዋነኛዉ ምክንያትም ይህ ሆነዉ ነዉ እንጂ የቋንቋዎች ንጉስ ሆነዉ አይደለም፡፡ 

መታየት ያለበት ሌለ ጉዳይ ደግሞ በተለይ በኦሮሚያ፣በደቡብ፣ በአፋር፣በሶማሌ፣በጋምቤላ፣በጉሙዝና በወዘተ ዙሪያ  የሚገኙ ከተሞቸ ዉስት በብዛት የሚኖሩ የአከባብ ተወላጆች አይደሉም፡፡ ዛሬም ብሆን በእነኚ የክልል ከተሞች ዉስጥ በብዛት የሚነገረዉ ቋንቋም አማርኛ ነዉ፡፡ አማሪኛ ለምን ተነገሬ ማለቴ አይደለም፤ ቋንቋ ሀብት ነዉና፡፡ እኔም አማርኛ በመቻሌ ነዉ ሀሳቤን በአማሪኛ እየገለጽኩኝ ያለሁት፡፡ ዋና ቁምነ ገሩ ግን  ማንኛዉም ሰዉ ወደ ፈለገበት ቦታ መሄድ፣መኖር፣መስራት፣መጉበኘትና ወዘተ ይችላል፡፡  ይህ ሰዉ ግን ወደ ፈለገበት ቦታ መሄድ፣መኖር፣መስራትና መጉበኘት የሚችለዉ የአከባቢዉን ሕብረተሰብ ቋንቋንና ባህልን በማይጎዳ መልኩ መሆን አለበት፡፡ ዛሬ ግን በሌሎችም ሆነ በአሮሚያ ክልል የሚናየዉ ነገር በጣም የሚገርም ነዉ፡፡ በአጼዎች ጊዜ አማርኛ እንደ የንጉስ ቋንቋ ተወስደዉ፣ ሌላዎቹን ግን የማንቋሸሽና የመናቅ አዝማሚያ ይታይ ነበረ፡፡ በኢትዮጵያ በቆዳ ስፋትም ሆነ በብሄር ብዛት ኦሮሚያና ኦሮሞ መሆኑን የሚክድ ሰዉ ያለ አይመስለኝም፡፡ ሆነዉም ግን የኦሮሞ ህዝብ ከአጼዎች ዘመን ጀሚሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከስርዓቱም ሆነ ከከተማ ያገኘ ጥቅም የለም፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ያገኘ ነገር ብነገር ከቦታ መፈናቀል፣ተመልሰዉ አገልጋያቸዉ መሆን፣የራሱን ቋንቋ ማጣት፣ሳይወድ በገዛ አገሩ የሌለ ብሄር ቋንቋና ባህል መቀበል (assimilation) ና የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡ 

የሚገርሚ ነገር ብኖር፣ እኔ ራሴ በአይኔ ያየሁት ነገር፣ አንዳንድ በኦሮሚያ ከተሞች ዉስጥ የተወለዱት ልጆች ኦሮሚኛ አለመቻላቸዉ ሳይሆንም የገረመኝ፣እናት አማርኛ አትችልም፤ ልጇ ደገሞ ኦሮሚኛ አትችልም፡፡ እንደዚህ አይነቱ የተዛባ ህብረተሰብ እስከ መቼ  ነዉ የሚንፈጥረዉ? ከላይ እንደ ጠቀስኩኝ ሁሉ፣ አሁንም ደገሜ እላለሁኝ፤ ማንኛዉም ሰዉ ወደ ፈለገበት ቦታ መሄድ፣መኖር፣መስራት፣መጉበኘትና ወዘተ ይችላል፡፡  በሰላማዊና በሰነጠለ ዓዕምሮ ሲናይ ይህ ሰዉ ግን ወደ ፈለገበት ቦታ መሄድ፣መኖር፣መስራትና መጉበኘት የሚችለዉ፣ የአከባቢዉን ሕብረተሰብ ቋንቋንና ባህልን በማይጎዳ መልኩ መሆን አለበት፡፡ በኦሮሚያ እያየን ያለነዉ ነግር ይሄን የሚቃረን ነዉ፡፡ እዉነት ብንናገር እኮ አርፍ ነዉ! ሌሎች ብሄር በኦሮሚያም ሆነ በሌሎች ክልሎች ሲኖሩ በነርሱ ቋንቋና ባህል ሊያስተዳደሩ አይችሉም፤እንድሁም ቋንቋችንና ባህላችንን ማጥፋትና መግደል የለባቸዉም፡፡ በባሕር ዳር፣ በጎንደርና በጎጀም በብዛት የሚኖረ ኦሮሞ ነዉ ወይስ አማራ ወይስ ትግሬ? በመቀሌ፣በአድዋና የመሳሰሉ ከተሞች ዉስጥ የኦሮሞ ህዝብ በነዋሪነት ይኖራልን? ወደ አሮሚያ ስንመጣስ፣ በሸገር፣በአዳማ፣በሻሻማኔ፣በአሰላ፣በድሬ ዳዋ፣ በነቀምት፣ በአዶላ፣ በጭሮ፣በያቤሎና በወዘተ የአማራ፣የትግሬ፣የደቡብ ብሄር ነዋሪ ብቆጠር እነርሱ ናቸዉ ወይስ ኦሮሞ ነዉ የሚበልጠዉ? አሁንም የሚገርማቹ ነገር፣ በብዙ የኦሮሚያ ከተሞች ዉስት የመዋለ-ሕጻናት ት/ቤት በአማርኛ እንጂ የኦሮሚኛ ማግኘት ያስቸግራል፡፡ 

ይህ በእንድ እንዳሌ፣ሌላ ብሔር ወደ ኦሮሚያ መጥተዉ ከኦሮሚያ ስጠቀም፣ ኦሮሞ ገግሞ ከቤት ንብረቱ ስፈናቀል፤ ለምሳሌ በድሮ ጀሚረዉ ለወንጂ ስኳር ፋብርካና ለሸንኮራ እርሻ ልማት ሰበብ የተፈናቀሉ ኦሮሞች፣ከተያየ ፋብርካ በሚወጣ መርዛማ ኬሚካሎች አከባብና ወንዞች  በተለይ አዲስ አባባ አከባቢ የሞጆ፣የአቃቂ፣የመቂንና ወዘተ  ሲመረዙ ማየት ይቻላል፡፡ ከአጼዎቹ ጊዜ ጀሚሮ በደቡብ ኦሮሚያ በጉጂ ዞን የሚትገኘዉን የአዶላና የሻኪሶ ወርቅ እያመረቱ አከባብዉ ግን ተበከለዉና ተጎሳቅለዉ ይገኛል፡፡ ዛሬም ብሆን በአዓመት 4.1 ቶን ወርቅ ከኦሮሚያ ከሻኪሶ ነዉ እየተመረተ በየወሩ በአዉሮፒላን እየተጫነ ነዉ ያለዉ፡፡ ኦሮሚያ ለኢትዮጵያ ልማት በእርሻ፣ በማዕድንና ወዘተ የጀርባ አጥንት ሲትሆን ኦሮሞ ግን ምን ተጠቀሜ ለሚለዉን ጥያቄ እንስሳ ካልሆነ በስተቀር ማሰብ የሚችል ሁሉ ማንሳቱ አይቀረ ነዉ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ፀረ-ልማትም አይደለም፤እንዶዉም የኢትዮጵያ የልማት አባት ነዉ እንጂ፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ለኢትዮጵያ ልማት ሲል የተጎዳ አሳዳጊ እንድሁም  የዋህና ጥሩ አባት ነዉ፡፡ የዋህነት ግን ሞኝነት አይደለም፤አልፈዉም ተርፈዉ በኦሮሞ መሬት ላይ እየተቀመጠ ኦሮሞን እንደ ሞኝ የሚዘልፉ አልጠፉም፡፡  

በልማት ሥም፣ ዛሬም ብሆን ኦሮሞ መሬቱን እየአጣ ነዉ፤ ኦሮሞ እየተጎዳ ነው፡፡ ኦሮሞ ልማትን አይጠላም፡፡ የኦሮሞን ማንነት፣ቋንቋ፣ባህልና ወዘተን የሚያጠፋ ግን ይጠላል! ብዙ ገበሬዎች በእንቨስትመንት ስም በትንሽ ካሳ ከመሬታቸዉ የተነሱት ግን ተመልሰዉ የባለ ሀብቶቹ አሽከር እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ ኢ.ሕ.አ.ግ. እራሱ በቀረጸዉ በፖሊሲ የሚለዉ  መሬቱ በገበሬ እጅ ስለሚገኝ መሬት ይሸጥ ይለመጥ ከተባሌ ገበሬዉ የባለብቶቸ አሽከር ሲለሚሆኑ፣ የመሬት ሽያጭ በኢ.ሕ.አ.ግ. መቃብር ላይ ነዉ ይላሉ፡፡ ነገር ግን የኢ.ሕ.አ.ግ. ካድሬዎች ያወጡትን ሕግ መልሰዉ አያፈረሱ ናቸዉ፡፡ በተለይ ወያኔዎቹ ብዙ ሀብት ካፈሩ በኋላ መሬት ይሸጥ ይለመጥ ይመስል በተለያዩ ቦታዎች በልመት ስም ገበሬዎቹን እያፈናቀሉ ለዉጪ ባለሀብቶች እየሸጡ ለራሳቸዉም መሬቱን እየተቆራመቱ ናቸዉ፡፡

ይህ የመሬት መቆራመት በዲስ አበባ ባሉት በኦሮሚያ ከተሞች ከተካሄደ በኋላ በልማት ስም አዲስ ፕላን በማዉጣት፣ የፊንፊኔ  ዙሪያ ልዩ ዞን ከተሞች ሁሉ በአዲስ አበባ ስር ገብተዉ መልማት አለበት ብለዉ የልማት ተቆርቋሪ ሆነዉ ብቂ ማለት ጀመሩ፡፡ ከዚህ በፍትም የወያኔ መንግስት የአዳማ ከተማ የኦሮሞ ዋና ከተማ ነዉ ብለዉ ኦሮሞን ከአዲስ አበባ ሲያስወጣ የዩኒቨሲቲ ተማረዎች ነቅተዉ ቢቃወሙም የገጠማቸዉ ግን መታሰርና ከትምህርታቸዉ መባርሩ ነዉ፡፡ በሚገርሚ ሁኔታ ግን በምርጫ 97 ጊዜ ቅንጅት በአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ምርጫዉን ሲያሸንፍ፣ ወያኔ ግን  “አዲስ አበባ አባት አላት፤የሀገሩ አባት ኦሮሞ ነዉ”  በማለት በእጁ የጠፈጠፈዉን ኦ.ሕ.ደ.ድ. ባንድ ማግስት ወደ አዲስ አበባ እንደመለሱ በነጋሪት ጠራ፡፡ 300 የሚሆኑ የኦሮሞ ተማሪዎች ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተባረሩትና የታሰሩት ተማሪዎች ከተጎዱ በኋላ እዉነት አገኙ ማለት ነዉ፡፡ የወያኔ መንግስት ይህን ያደረገበት  ዋንኛዉ ምክንያት፣ በአማራ ህዝብና በኦሮሞ ህዝብ መኃከል ጥላቻን በመዝራት እድሜዉን ለማዛረም እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በኢ.ፈ.ዲ.ረ. ሕገ-መንግስት አንቀጽ ፵፺/፶ 49/5 ላይ የሚለዉ የኦሮሞ ህዝብ ከአዲስ አበባ ልዪ ጥቅም ማግኘት አለበት ይላል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ እንኳን ልዪ ትቅም ከማግኘት ሌሎቹ ኢትዮጵያዉይን ያገኙት ጥቅም አላገኘም፡፡  ከዚህ በፊትም የወያኔ መንግስት የአዳማ ከተማ የኦሮሞ ዋና ከተማ ነዉ ብለዉ ኦሮሞን ከአዲስ አበባ ሲያስወጣና  የዩኒቨሲቲ ተማረዎች ነቅተዉ ቢቃወሙም፣ ኦ.ሕ.ደ.ድ ትዕዛዙን ተቀብሎ ሲሄድ፣  በምርጫ 97 ጊዜ ቅንጅት በአዲስ ሙሉ በሙሉ ሲያሸንፍ፣ ወያኔ  “አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት፤ ሀገር አባት አላት፤የሀገሩ አባት ኦሮሞ ነዉ”  በማለት በእጁ የጠፈጠፈዉን ኦ.ሕ.ደ.ድ. ባንድ ማግስት ወደ አዲስ አበባ ስለ ጠራ፣ ይህ የፖሊትካ ቁማር ብዙዎችንና ወኔ ያላቸዉ ኦ.ሕ.ደ.ድ.ዎችን አናደድዉ ነበር፡፡ የወያኔ መንግስት  በልማት ስም አዲስ ፕላን በማዉጣት የፊንፊኔ  ዙሪያ ልዩ ዞን ከተሞች ሁሉ በአዲስ አበባ ስር አገብቸ አለመለሁ ብለዉ በልማት ስም የልማት ተቆርቋሪ ሆነዉ  በአዲስ አበባ ነገር ለ2ኛ ጊዜ ብቂ ሲል በብዙዎቹ ዘንድ ከዚህ በፍት በአዲስ አበባ ስም የተቆመረ ቁማር ትዝ ሲላቸዉ፣ ወያኔ ባልጠቀ መልኩ እንኳን ኬዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይቅርና ከአ.ሕ.ደ.ድ. አበላትም ተቃዉሞ ገጠመዉ፡፡

የወያኔ መንግስት በኦነግ ለይ በሰራ ሴራ፣ ኦነግን ከሀገር ካስወጣ በኋላ፣ አባት እንደሌላቸዉ ልጆች በኦሮሞ ህዝብ ከሀያ ዐመታት በላይ ብጫወትበትም፣ ኦነግ በቀረጸዉ ቁቤ ወይም ፊደል የተማርነዉ የቁቤ ትዉልደችና የተጨቆነ የኦሮሞ ህዝብ ሁሉ ወደ ኦነግነት ተቀይሯል፡፡ ኦነግ የለም ብሎ ወያኔ ብጨፍርብንም ግድያ፣ እስራት፣ ጭቆና፣ ግርፋት፣ስደት፣ድህነትና ወዘተ ያማረራቸዉ  የኦሮሞ ሕዝብ ሁሉ ለራሳቸዉ በራሳቸዉ ባሁኑ ጊዜ ወደ ኦነግነት ተለዉጧል፡፡ 

የወያኔ መንግስት ብሄር-በረሰቦችትን እያጋጨ፣ በተልይ በኦሮሞና በአማራ መሓል ቁማር እየተጫወተ መኖር ይፈልጋል፡፡ ይህ የወያኔ ሴራ በዚህ ብቻ አላበቃም፤ በልማት ስም አዲስ ፕላን በማዉጣት የፊንፊኔ  ዙሪያ ልዩ ዞን ከተሞች ሁሉ በአዲስ አበባ ስር አስገብቸ አለመለሁ የሚለዉ የወያኔ መንግስት፣ ከፒላኑ በስተጀርባ ሌላ ሴራ ማሴሩን ደርሰንበታል፡፡ ከዚህ በፊትም እንዳልኩኝ የኦሮሞ ሕዝብ ፀረ-ልማትም አይደለም፤እንዶዉም የኢትዮጵያ የልማት አባት ነዉ እንጂ፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ለኢትዮጵያ ልማት ሲል የተጎዳ አሳዳጊ እንድሁም  የዋህና ጥሩ አባት ነዉ፡፡ በልማት ሥም፣ ዛሬም ብሆን ኦሮሞ መሬቱን እየአጣ ነዉ፤ ኦሮሞ እየተጎዳ ነው፡፡ ኦሮሞ ልማትን አይጠላም፡፡ የኦሮሞ ማንነት፣ቋንቋ፣ባህልና ወዘተን የሚያጠፋ ልማት  ግን ኦሮሞ አይወድም!

የወያኔ መንግስት ያሴረዉ ሴራ፣ በአዲስ አበባና በዲስ አባባ ዙሪያ ብዙ ንብረት ሲላፈራ፣ የኦሮሞ ገበሬዎችን ከመሬጣቸዉ እያፈናቀለ አዲስ አባባን ከሌላ ክልል ጋር በማገናኘት፣ አዲስ አበባን ከኦሮሞ ህዝብ እጅ በማዉጣት ኦሮሞና አማራን በማጋጨት እጁን ታጥቦ ለመብለት ተዘጋጅቷል፡፡ በተለይ አዲስ አበባ ከደብረ ብርን ከተማ 60 ኪ.ሜ. ብቻ ሲለሚትርቅ፣ የወያኔ ሴራ ቀስ በቀስ  በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉት ከተሞችን ከኦሮሚያ ግዛት እያነጠቀ ኦሮሚኛን የሚትገልና አማርኛና ትግርኛን  የሚታወራ አዲስ አበባን ከደብረ ብርን ጋር ማገናኘት ነዉ፡፡ ከዚያም አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት ባለዉ አፉ፣ ወያኔ አዲስ አበባን ከአማራ ክልል ጋር አገናኝተዉ የአማራ ነዉ ብለዉ፣ እኛ ሲንባላ ለራሱ ዘና ብለዉ ለመኖር እንደፈለገ ታዉቋል፡፡ አንድ የኦሮሚኛ ተረት እንደምለዉ፣ “qoreen qoree hin waraantu, namni qoree lamaan wal-waraansisuuf yaale ofumaaf waraannama” ትርጉሙም፣ ሁለት እሾኮች አይወጋጉም፣ ሁለት እሾኮችን ለማወጋጋት የሞከረ ሰዉ ለራሱ ይወጋል ማለት ነዉ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ማለት የሚፈልገዉ ነገር ቢኖር፣ በሰብዓዊ ሕሊና አማራና ኦሮሞ በወያኔ ሴራ በመንቃት አብረዉ የወያኔ መንግስት ለመጣልና ነጻነት ለማግኝት መታገል አለባቸዉ ባይ ነኝ፡፡ ኦሮሞ ሲጨፈጨፍ አማራ አይመለከተኝም ማለት የለበትም፡፡ አማራም ሲጨፈጨፍ ኦሮሞም ዝም ማለት የለበትም፡፡ ይህን ከላደረግን በ21ኛ ክፍለ ዘመን ዉስጥም የጥያቄያችን መልስ እንደሚናየዉ ጥይት ይሆናል፡፡



በጣም የገረመኝ ነገር ሌላ ነግር ብኖር፣ በንጉሱ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች  ያሰሙ የነበሩ መፈክርና ሰሞኑ እያሰሙ ያሉት  መፈክር አንድ አይነት ነዉ፡፡ በንጉሱ ጊዜ የነበሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሬት ለአራሹ እያሉ ነበረ፤ ሰሞኑም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ገበሬዎች ከመሬታቸዉ እንዳይፈናቀሉ! መሬቱ የገበሬ ነዉ እያሉ ነበር፡፡በዚያን ጊዜ ከተቀረጹት ፊልሞች መመልከት እንደ ቻልኩኝ፣ በንጉሱ ጊዜ የነበሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰለማዊ ሰልፍ ሲወጡ፣በዚያን ጊዜ የነበሩ ፖሊሶች ለተማርዎች የጥይት መልስ አልመለሱም፡፡ ዛሬ ግን ወያኔ በ21ኛ ክፍለ ዘመን የጥይት መልስ እየሰጠ፣ በጠራራ  ፀሃይ በአምቦ፤በባሌ፣በጉደር፤በነቀምት፣ በሻምቡ፣በጊምብ፣በነጆ፣በአይራ፣በደምቢ ዶሎ፣በሴላሌና ወዘተ  በመቶዎቹ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሲገድል፣ በጎንደር አከባብም 6 ሰዎችን ተኩሰዉ መግደሉ ተሰምተዋል፡፡ አንዳደም ወታደሮቹ ጦር ሜዳ መስላቸዉ መሰላማዊ ዜጎች ለይ የተኩስ እሩምታ ሲከፍቱ፣አገሪቱ በወታደሮች ብቻ ነዉ እነደ የሚትተዳደረዉ ያስብላል፡፡

ሃሳቤን ባጭሩ ለመቋጨት፣ የኦሮሞ ሕዝብ ልማትን ጠልተዉ አይደለም የፊንፊኔ ዙሪያ የልዩ ዞን አዲስ አበባ ስር መግባትን የጠላ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ከዚህ በኋላ የወያኔን ቃል የሚያምንበት ልብ አጥቷል፡፡ እስት ሕሊና ያለዉ የኢትዮጵያ ልጅ ሁሉ ከዚህ በፊት ወያኔ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሰራዉን ተንኮል በማሰብ በኦሮሞ ቦታ ሆነዉ ይፍረድ! እኔ በበኩሌ አላምንም፡፡ በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኙ እስር ቤቶች፣ በነርሱ ቋንቋ ማረሚያ ቤቶች 90 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች  የኦሮሚኛ ቋንቋ ተናጋሪ ነዉ ይባላል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ የዋሕና ለሌሎች ሕዝቦች የሚራራና ከወንጀል ጋርም የሚያስተሳስረዉ ነገር እነደሌለ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያዉቃል፡፡ የወያኔ መንግስት ግን ኦሮሞን ሲለ ፈራ ብቻ ስልጣን በጨበጠዉ አጋጣሚ ተጠቅሞ፣ በኦሮሞቹ ለይ የፈጸሜ ሴራ ሲያንሰዉ፣  ጨፍጭፈዉና አስረዉ መጨረስ አቅቶታል፡፡

ባጭሩ የኦሮሞ ሕዝብ ልማትን አይጠላም፤እሺ እዉነትም፣ ነገሩ ለልማት ከሆነ፣ የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞንን ከኦሮሚያ ክልል ማስተዳደር ሥር ለምን ማዉጣት ፈለጉ? ድረዉም ሁሉም ነገር በነርሱ ትዕዛዝ እንደሚከናዉን እናዉቃለን፡፡ ኦሮሚያ ሲር ሆና መልማት አትችልም ነበር? ኦሮሚያ ልማት ለይ አይደለችም ማለታቸዉ ነዉ? አንድ የኦሮሚኛ ተረት እንደሚለዉ፣ “bineensi bosona keessaa gugatu/fiigu kan ciisu kaasaa” ይላል፡፡ ትርጉሙም፣ከጫካ ዉስጥ ተነስቶ የሚሮጥ አዉሬ ሌላ የተኛዉን አዉሬ ያስነሳል ማለት ነዉ፡፡ ተረቱም እንደሚያሳየን በግድያ፣በእስራት፣በግርፊያ፣በመገልለ፣ፊትሕ በማጣት፣ በድህነት፡ በስራ አጥነት፣ ተምረዉ በመናቁና በወዘተ የተማረሩ የኦሮሞ ተወላጆች ለፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ከኦሮሚያ መስተዳደር ሥር እንድ ወጡና አዲስ አበባ ስር ማስገባት የተባለዉን ፒላን ለዬኒቭርሲቲ ተማርዎች  በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ጥይት መልስ ሆነዉ ስለ ተመለሰላቸዉና  በወያኔ መንግስት የተማረረ ሕዝብ የተቃዉሞዉ ሰልፉን ወደ ሕዝባዊ አመጽ ቀይሮታል፡፡ ሎሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ አንዲነት ለፊትሕና ለዲሞኪራሲ ፓርቲ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ባደረገዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እዳስታወቀ፣ የወያኔ መንግስት በኦሮሞቹ ላይ እያደረገ ያለዉ ጭፍጨፋ ያሳዘናቸዉና አጥብቀዉም እንደሚቃወሙ ተናገሯል፡፡ 

የወያኔ መንግስት ከዚህ በፊትም አማራዎችን፣ አኟኮችን፣ጉሙዞችን፣ ደቡቦችን ፣አፋሮችን፣ሶመሌዎችንና ወዘተን ሰለጨፈጨፈ ፊትሕ የሚትፈልግ ኢትዮጵያዊ ሁሉ፣ ባገር ዉስጥም ሆነ በዉጪ የሚትገኝ ተጨቋኝ ህዝቦች ሁሉ በኦሮሚያ ክልል በሁሉም ቦታ የተጀመረ የኦሮሞን አመጽ በመደገፍ በወያኔ መንግስት ላይ ተቃዉሞዉችሁን እንዲታቀርቡ ኢትዮጵያቂ ጥሪዬን አቀርባለሁኝ፡፡ ድል ለሰፍዉ ሕዝብ!




















































































0 Comments:

Post a Comment

Subscribe to Post Comments [Atom]

<< Home